የግርጌ ማስታወሻ
b ጠርጡለስ፣ ለሕዝቡ “ብዙ ሰላም” በማምጣቱ ፊሊክስን አመስግኖታል። ይሁን እንጂ የፊሊክስን የግዛት ዘመን ያህል ሰላም የጠፋበት የሮም አገረ ገዢዎች ዘመን የለም፤ ከፊሊክስ ዘመን የከፋ ብጥብጥ የታየው በሮም ላይ ዓመፅ በተነሳበት ጊዜ ብቻ ነው። ጠርጡለስ፣ ፊሊክስ ላስገኘው መሻሻል አይሁዳውያን “ታላቅ ምስጋና” እንዳቀረቡ መናገሩም ዓይን ያወጣ ውሸት ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ አብዛኞቹ አይሁዳውያን ፊሊክስን ይጠሉት ነበር፤ ፊሊክስ ጨቋኝ ገዢ ከመሆኑም ሌላ ዓመፅን ለማስቆም የሚወስደው እርምጃ ጭካኔ የተሞላበት ነበር።—ሥራ 24:2, 3