የግርጌ ማስታወሻ
b በዚህ ሕግ ውስጥ የተካተተው አስደናቂ ዝግጅት ሩት በትውልድ አገሯ ከምታውቀው ፈጽሞ የተለየ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። በዚያ ዘመን በመካከለኛው ምሥራቅ መበለቶች በደል ይደርስባቸው ነበር። አንድ የማመሳከሪያ ጽሑፍ እንዲህ ይላል፦ “አንዲት ሴት ባሏ ከሞተ በኋላ በአብዛኛው ደጋፊና ጧሪ የሚሆኗት ወንዶች ልጆቿ ነበሩ፤ ወንዶች ልጆች ከሌሏት ግን ያላት አማራጭ ራሷን ለባርነት መሸጥ፣ ዝሙት አዳሪ መሆን አለዚያም መሞት ነበር።”