የግርጌ ማስታወሻ
c ቦዔዝ ለሩት ስድስት መስፈሪያ (መለኪያው አልተገለጸም) ገብስ መስጠቱ፣ ከስድስት የሥራ ቀናት በኋላ የሰንበት እረፍት እንደሚኖር ሁሉ ሩትም በመበለትነት ያሳለፈችው የልፋት ዘመን አብቅቶ ባል ማግባትና ኑሮ መመሥረት የሚያስገኘውን እረፍት የምታጣጥምበት ጊዜ እንደቀረበ ለመጠቆም ብሎ ሊሆን ይችላል። በሌላ በኩል ደግሞ ምናልባትም በላይዳ እየዛቀ የሰጣት ገብስ ስድስት መስፈሪያ ብቻ የሆነው ሩት ከዚያ በላይ ልትሸከም ስለማትችል ሊሆን ይችላል።