የግርጌ ማስታወሻ
c ዘገባው ካህናቱ የሚቀርቡትን መሥዋዕቶች ይንቁ እንደነበር የሚያሳዩ ሁለት ምሳሌዎችን ይዟል። በመጀመሪያ ደረጃ፣ ሕጉ ከመሥዋዕቱ ውስጥ የካህናቱ ድርሻ የትኛው እንደሆነ ለይቶ ይገልጽ ነበር። (ዘዳ. 18:3) ክፉዎቹ ካህናት ግን በማደሪያ ድንኳኑ ውስጥ ከዚህ በጣም የተለየ አሠራር ይከተሉ ነበር። ካህናቱ፣ ሥጋው እየተቀቀለ ሳለ አገልጋዮቻቸውን በመላክ ከድስቱ ውስጥ ማንኛውንም ምርጥ ሥጋ በሜንጦ አውጥተው እንዲያመጡላቸው ያደርጉ ነበር! ሌላው ደግሞ ሰዎቹ መሥዋዕታቸውን በመሠዊያው ላይ እንዲቃጠልላቸው ሲያመጡ ክፉዎቹ ካህናት የመሥዋዕቱ ስብ ገና ለይሖዋ ከመቅረቡ በፊት አገልጋያቸው መሥዋዕት ከሚያቀርበው ሰው ላይ ጥሬ ሥጋ ነጥቆ እንዲያመጣላቸው ያደርጉ ነበር።—ዘሌ. 3:3-5፤ 1 ሳሙ. 2:13-17