የግርጌ ማስታወሻ
a የዚህ “ለስለስ ያለ ድምፅ” ምንጭ በ1 ነገሥት 19:9 ላይ የተጠቀሰውን የይሖዋን “ቃል” እንዲያደርስ የተላከው መንፈሳዊ አካል ራሱ ሳይሆን አይቀርም። በቁጥር 15 (NW) ላይ ይህ መንፈሳዊ አካል “ይሖዋ” ተብሎ ተጠርቷል። ይህም ይሖዋ እስራኤላውያንን በምድረ በዳ ለመምራት የተጠቀመበትንና “ስሜ በርሱ ላይ ነው” በማለት የተናገረለትን መንፈሳዊ አካል ያስታውሰን ይሆናል። (ዘፀ. 23:21) እውነት ነው፣ ስለዚህ ጉዳይ በእርግጠኝነት መናገር አንችልም፤ ያም ሆኖ ኢየሱስ ሰው ከመሆኑ በፊት “ቃል” ማለትም ለይሖዋ አገልጋዮች ልዩ ቃል አቀባይ ሆኖ እንዳገለገለ ልብ ማለት ይገባል።—ዮሐ. 1:1