የግርጌ ማስታወሻ
a ዮናስ የተወለደው በገሊላ በምትገኝ ከተማ ውስጥ መሆኑ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፤ ምክንያቱም ፈሪሳውያን በአንድ ወቅት ስለ ኢየሱስ ሲናገሩ በእብሪተኝነት መንፈስ “ከገሊላ አንድም ነቢይ እንደማይነሳ መርምረህ ተረዳ” ብለው ነበር። (ዮሐ. 7:52) በርካታ ተርጓሚዎችና ተመራማሪዎች እንደገለጹት ፈሪሳውያን ዝቅ ተደርጋ ከምትታየው ከገሊላ ነቢይ ተነስቶ አያውቅም፣ ወደፊትም አይነሳም የሚል ጭፍን አመለካከት ነበራቸው። ይህ እውነት ከሆነ ፈሪሳውያን ታሪክንም ሆነ ትንቢትን ወደ ጎን ገሸሽ አድርገው ነበር ማለት ነው።—ኢሳ. 9:1, 2