የግርጌ ማስታወሻ
a ንጉሡ፣ አይሁዳውያን በጠላቶቻቸው ላይ የተቀዳጁትን ድል እንዲያጠናቅቁ ተጨማሪ ቀን ፈቀደላቸው። (አስ. 9:12-14) በዛሬው ጊዜም እንኳ አይሁዳውያን በየዓመቱ አዳር በተባለው ወር ላይ ይህን ድል ያገኙበትን ቀን ያከብራሉ፤ ይህ ወር በየካቲት ወር መገባደጃና በመጋቢት ወር መጀመሪያ ላይ ይውላል። ይህ በዓል ፉሪም ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ስያሜውን ያገኘው ሐማ እስራኤላውያንን ለመደምሰስ ከጣለው ዕጣ ነው።