የግርጌ ማስታወሻ a በዚህ ዘገባና ማርያም ኤልሳቤጥን ለመጠየቅ ‘ተነስታ እንደሄደች’ በሚገልጸው ታሪክ መካከል ያለውን ልዩነት ልብ በል። (ሉቃስ 1:39) በዚያን ወቅት ማርያም የታጨች ብትሆንም ከዮሴፍ ጋር ገና ስላልተጋቡ እሱን ሳታማክር ሄዳ ሊሆን ይችላል። ከተጋቡ በኋላ ግን ማርያምና ዮሴፍ አብረው የተጓዙ ቢሆንም እንኳ ጉዞውን እንዳደረገ ተደርጎ የተገለጸው ዮሴፍ እንጂ ማርያም አይደለችም።