የግርጌ ማስታወሻ
c ላሜሕ ለልጁ ኖኅ የሚል ስም ያወጣለት ሲሆን ትርጉሙ “እረፍት” ወይም “መጽናኛ” ማለት ሊሆን ይችላል፤ በተጨማሪም ላሜሕ፣ ኖኅ በተረገመችው ምድር ላይ የሰውን ዘር ከድካሙ በማሳረፍ ከስሙ ትርጉም ጋር የሚስማማ ተግባር እንደሚፈጽም ትንቢት ተናግሯል። (ዘፍ. 5:28, 29) ሆኖም ላሜሕ ቀደም ብሎ በመሞቱ ይህ ትንቢት ሲፈጸም ማየት አልቻለም። የኖኅ እናት እንዲሁም ወንድሞቹና እህቶቹ በጥፋት ውኃው ጠፍተው ሊሆን ይችላል።