የግርጌ ማስታወሻ
c ቀደም ሲል የተሰጡት እንዲህ ያሉ ማስጠንቀቂያዎች ኃይል እንዳይኖራቸው ተጽዕኖ ያሳደረው አንዱ ምክንያት ማስጠንቀቂያዎቹ በዋነኝነት የሚሠሩት 144,000ዎቹን ላቀፈው የክርስቶስ ትንሽ መንጋ እንደሆነ ይታሰብ የነበረ መሆኑ ነው። ከ1935 በፊት በራእይ 7:9, 10 ላይ የተጠቀሰው “እጅግ ብዙ ሕዝብ” ስፍር ቁጥር የሌላቸውን የሕዝበ ክርስትና አብያተ ክርስቲያናት አባላት እንደሚያጠቃልል ተደርጎ ይታሰብ እንደነበር በምዕራፍ 5 ላይ እንመለከታለን፤ እነዚህ ሰዎች በመጨረሻው ቀን ከክርስቶስ ጎን ስለሚቆሙ ሁለተኛ ደረጃ የሚሰጣቸው የሰማያዊ ክፍል አባላት የመሆን ሽልማት እንደሚያገኙ ተደርጎ ይታመን ነበር።