የግርጌ ማስታወሻ b በአሁኑ ወቅት እነዚህ ዓመታት ብዙ መስለው ቢታዩንም በዚያን ዘመን የነበሩት ሰዎች ዕድሜ በጣም ረጅም እንደነበረ መዘንጋት አይኖርብንም። ለምሳሌ አዳም፣ የኖኅ አባት ላሜሕ እስከኖረበት ዘመን ድረስ ኖሯል። ላሜሕ፣ የኖኅ ልጅ ሴም እስከኖረበት ዘመን ድረስ ኖሯል። ሴም ደግሞ አብርሃም እስከኖረበት ዘመን ድረስ ኖሯል። በመሆኑም ከአዳም እስከ አብርሃም ዘመን ድረስ ያለፈው የጊዜ ርዝማኔ የአራት ሰዎች ዕድሜ ያህል ነው።—ዘፍ. 5:5, 31፤ 9:29፤ 11:10, 11፤ 25:7