የግርጌ ማስታወሻ
b “ቅናት” የሚለው ቃል የተሠራበት መንገድ ይሖዋ ለእሱ ታማኝ የመሆንን ጉዳይ ምን ያህል አክብዶ እንደሚመለከተው ያሳያል። ይህ ቃል አንድ ባል ሚስቱ ለእሱ ያላትን ታማኝነት ብታጓድል ምን ያህል እንደሚቆጣ ሊያስታውሰን ይችላል። (ምሳሌ 6:34) ልክ እንደዚህ ባል ሁሉ ይሖዋም የቃል ኪዳን ሕዝቦቹ ጣዖት በማምለክ ለእሱ የነበራቸውን ታማኝነት ሲያጓድሉ መቆጣቱ የሚያስገርም አይደለም። አንድ የማመሣከሪያ ጽሑፍ እንዲህ ይላል፦ “የአምላክ ቅናት . . . የሚመነጨው ከቅድስናው ነው። እሱ ብቻ ቅዱስ ስለሆነ . . . ማንም አምልኮውን እንዲቀናቀነው አይፈቅድም።”—ዘፀ. 34:14