የግርጌ ማስታወሻ
b እስራኤላውያን ብረት የማቅለጥን ሥራ ለምደው ነበር። ከመዳብ ማዕድን ማውጫ ቦታዎቻቸው የአንዳንዶቹ ቅሪት ተገኝቷል። እንዲሁም ለቤተ መቅደሱ የሚያገለግሉ መሣሪያዎችን ለማዘጋጀት ሲባል መዳብ ይቀልጥ ነበር። (ከ1 ነገሥት 7:14–46 ጋር አወዳድር) ይህ የማቅለጥ ሂደት በጭስ፣ በሚነጠርበት ጊዜ ከላይ በሚንሳፈፉ ቆሻሻዎችና በዝቃጮች መልክ የተወሰነ መጠን ያለው ብክለት ሳይፈጥር ይከናወን ነበር ማለት ሊሆን የማይችል ነገር ይመስላል። ሆኖም ይሖዋ አነስተኛ የሕዝብ ብዛት ባለበትና ገለልተኛ በሆነው አካባቢ ሊኖር የሚችለውን ቆሻሻ ችሎ ለማለፍ ፈቃደኛ እንደነበር ግልጽ ነው።