የግርጌ ማስታወሻ a ገላትያ 2:3 ቲቶ ግሪካዊ (ሔለን) እንደሆነ ይገልጻል። ይህ አባባል ቲቶ የግሪክ ተወላጅ መሆኑን ሊያመለክት ይችላል። ሆኖም አንዳንድ የግሪክ ጸሐፊዎች በውልደት ሳይሆን በቋንቋና በባሕል ግሪካዊ የሆኑ ሰዎችን ለማመልከት በብዙ ቁጥር (ሔለኒስ) ይጠቀሙ እንደነበር ይነገራል። ቲቶ ግሪካዊ የሆነው ከዚህ አንጻር ሊሆንም ይችላል።