የግርጌ ማስታወሻ
c ፕሮፌሰር ግሬትስ ሂስትሪ ኦቭ ዘ ጁውስ በተባለው መጽሐፋቸው ላይ አንዳንድ ጊዜ ሮማውያን በቀን 500 እስረኞችን ይሰቅሉ ነበር ብለዋል። ሌሎች ምርኮኛ አይሁዶች ደግሞ እጃቸውን ከተቆረጡ በኋላ ወደ ከተማዋ ይላኩ ነበር። እዚያስ ምን ዓይነት ሁኔታ ሰፍኖ ነበር? “ገንዘብ ዋጋውን በማጣቱ ዳቦ መግዛት አይችልም ነበር። ሰዎች እጅግ አስጸያፊ ለሆነ ምግብ፣ እፍኝ ለማይሞላ የሣር ድርቆሽ፣ ለቁራጭ ቆዳ ወይም ለውሾች የሚጣል ትርፍራፊ ለማግኘት በየመንገዱ ይሻሙ ነበር። . . . በየሜዳው የሚረፈረፈው አስከሬን ሞቃታማውን የበጋ አየር በተላላፊ በሽታዎች በክሎት የነበረ ሲሆን ሕዝቡም በበሽታ፣ በረሃብና በሰይፍ አለቀ።”