የግርጌ ማስታወሻ
b ይሖዋ ራሱ ተመሳሳይ የሆነ የመጸየፍ ስሜት አለው። ለምሳሌ ያህል ኤፌሶን 4:29 ጸያፍ አነጋገርን “ብልሹ ቃል” በማለት ይገልጸዋል። “ብልሹ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል የበሰበሰን ፍሬ፣ ዓሣ ወይም ሥጋ ያመለክታል። ይህ መግለጫ ክፉ ቃልን ወይም ጸያፍ አነጋገርን በተመለከተ ሊኖረን የሚገባንን የመጸየፍ ስሜት ሕያው አድርጎ ይገልጻል። በተመሳሳይም በቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ ጣዖታት ብዙውን ጊዜ እንደ “አዛባ” ተደርገው ተገልጸዋል። (ዘዳግም 29:17 NW፤ ሕዝቅኤል 6:9 NW) ለአዛባ ወይም ለዕዳሪ በተፈጥሮ ያለን የመጸየፍ ስሜት አምላክ ማንኛውንም የጣዖት ዓይነት ምን ያህል እንደሚጸየፍ እንድናስተውል ይረዳናል።