የግርጌ ማስታወሻ
a ዘ ጀሩሳሌም ባይብል ዘፍጥረት 2:17ን አስመልክቶ ባሰፈረው የግርጌ ማስታወሻ ላይ ‘መልካምንና ክፉን ማወቅ’ የሚለውን አባባል “ምን ነገር መልካም፣ ምን ነገር መጥፎ እንደሆነ የመወሰንና በዚያ መሠረት የመመራት ሥልጣን ማለትም የሰው ልጅ ፍጡር መሆኑን ለመቀበል አሻፈረኝ ብሎ ሙሉ በሙሉ በራስ ለመተዳደር ያደረገው ምርጫ” በማለት ይገልጸዋል። አክሎም “የመጀመሪያው ኃጢአት በአምላክ ሉዓላዊነት ላይ የተሰነዘረ ጥቃት ነበር” ይላል።