የግርጌ ማስታወሻ
a የገንዘብ ሚኒስትር የነበሩት ሳመን ፒ ቼዝ ኅዳር 20, 1861 ለዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ማተሚያ ድርጅት እንዲህ የሚል ደብዳቤ ጽፈው ነበር:- “ማንኛውም አገር ቢሆን ያለ አምላክ እርዳታ ጠንካራ መሆን ወይም ያለ እርሱ ጥበቃ ደህንነት ማግኘት አይችልም። ሕዝባችን በአምላክ እንደሚታመን በአገራችን ሳንቲሞች ላይ መገለጽ አለበት።” በዚህም ምክንያት “በአምላክ እንታመናለን” የሚለው መርሕ በአሜሪካ የመገበያያ ሳንቲሞች ላይ በ1864 ለመጀመሪያ ጊዜ ወጣ።