የግርጌ ማስታወሻ c አንዳንድ ምሁራን የድንቢጧ መውደቅ መሞቷን ብቻ የሚያመለክት ላይሆን እንደሚችል አስተያየት ይሰጣሉ። ጥቅሱ በመጀመሪያ በተጻፈበት ግሪክኛ ቋንቋ የተጠቀሰው ቃል ወፏ ምግብ ለመለቃቀም መሬት ላይ ማረፏን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል ይላሉ። ይህ አባባላቸው እውነት ከሆነ አምላክ የወፏን መሞት ብቻ ሳይሆን ለምታደርገው ዕለታዊ እንቅስቃሴ ትኩረት ይሰጣል እንዲሁም ያስብላታል ማለት ነው።—ማቴዎስ 6:26