የግርጌ ማስታወሻ
a መጽሐፍ ቅዱስ “ብርሃን” የሚለውን ቃል በተለያዩ ምሳሌያዊ መንገዶች ይጠቀምበታል። ለምሳሌ ያህል፣ መጽሐፍ ቅዱስ አምላክን ከብርሃን ጋር አያይዞ ይገልጸዋል። (መዝሙር 104:1, 2፤ 1 ዮሐንስ 1:5) በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኘው መንፈሳዊ እውቀት በብርሃን ተመስሏል። (ኢሳይያስ 2:3-5፤ 2 ቆሮንቶስ 4:6) ኢየሱስ ምድራዊ አገልግሎቱን ባከናወነበት ወቅት ብርሃን ነበር። (ዮሐንስ 8:12፤ 9:5፤ 12:35) እንዲሁም የኢየሱስ ተከታዮች ብርሃናቸውን እንዲያበሩ ታዘዋል።—ማቴዎስ 5:14, 16