የግርጌ ማስታወሻ a በዚህ ዘገባና ማርያም ኤልሳቤጥን ለመጠየቅ ‘ተነሥታ እንደሄደች’ በሚገልጸው ታሪክ መካከል ያለውን ልዩነት ልብ በል። (ሉቃስ 1:39) ወደ ኤልሳቤጥ በሄደችበት ጊዜ ማርያም የታጨች ብትሆንም ከዮሴፍ ጋር ገና ስላልተጋቡ እሱን ሳታማክር ሄዳ ሊሆን ይችላል። ከተጋቡ በኋላ ግን ማርያምና ዮሴፍ አብረው የተጓዙ ቢሆንም እንኳ ጉዞውን አስመልክቶ ውሳኔ ያደርግ የነበረው ዮሴፍ እንደሆነ ተገልጿል።