የግርጌ ማስታወሻ
a እርግጥ ነው፣ ኢየሱስ “የሰማይ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ” ብሏል። (ማቴ. 5:48) ኢየሱስ፣ ፍጽምና የጎደላቸው ሰዎችም እንኳ በአንጻራዊ ሁኔታ ሙሉ ወይም ፍጹም መሆን እንደሚችሉ ተገንዝቦ ነበር። በእርግጥም ሰውን ሁሉ እንድንወድ የተሰጠንን ትእዛዝ መፈጸም እንችላለን፤ እንዲህ በማድረግም አምላክን እናስደስታለን። ከእኛ በተቃራኒ ግን ይሖዋ ሙሉ በሙሉ ፍጹም ነው። “ንጹሕ አቋም” የሚለው ቃል ከይሖዋ ጋር በተያያዘ ሲሠራበት ፍጹም መሆንንም ይጨምራል።—መዝ. 18:30