የግርጌ ማስታወሻ b ሰብዓ ሊቃናት፣ ዮናስ በተኛበት ወቅት እንዳንኮራፋ በመግለጽ ምን ያህል ከባድ እንቅልፍ ወስዶት እንደነበር ይጠቁማል። ይሁንና ዮናስ መተኛቱ ግዴለሽ እንደነበር የሚያሳይ ምልክት ነው ብለን መደምደም የለብንም፤ ከዚህ ይልቅ አንዳንዶች ስሜታቸው በጣም በሚደቆስበት ጊዜ በእንቅልፍ ሊሸነፉ እንደሚችሉ ማስታወስ ይኖርብናል። ኢየሱስ በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ በጣም ተጨንቆ በነበረበት ወቅት ጴጥሮስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ “ከሐዘን የተነሳ ሲያንቀላፉ” ነበር።—ሉቃስ 22:45