የግርጌ ማስታወሻ
c ኢየሱስ ክርስቶስና ሐዋርያቱ በነበሩበት ዘመን ሁሉም የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት በግሪክኛ ተተርጉመው ነበር። ይህ ትርጉም ሰብዓ ሊቃናት የሚባል ሲሆን ግሪክኛ ተናጋሪ የሆኑ አይሁዳውያን በስፋት ይጠቀሙበት ነበር። በክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ከሚገኙትና ከዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት በቀጥታ ከተወሰዱት በመቶዎች የሚቆጠሩ ጥቅሶች አብዛኞቹ ከሰብዓ ሊቃናት ትርጉም የተወሰዱ ናቸው።