የግርጌ ማስታወሻ
a ኢያሱ ሲፈጸሙ በዓይኑ ከተመለከታቸው ተስፋዎች መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፦ ይሖዋ ለእስራኤላውያን የራሳቸው የሆነ ምድር እንደሚሰጣቸው የገባው ቃል (ዘፍጥረት 12:7ን ከኢያሱ 11:23 ጋር አወዳድር)፣ ከግብፅ ነፃ እንደሚያወጣቸው የሰጠው ተስፋ (ዘፀአት 3:8ን ከ12:29-32 ጋር አወዳድር) እንዲሁም ሕዝቡን እንደሚንከባከብ የገባው ቃል ናቸው።—ዘፀአት 16:4, 13-15ን ከዘዳግም 8:3, 4 ጋር አወዳድር።