የግርጌ ማስታወሻ
b ከአዋልድ መጻሕፍት ጋር በተያያዘ ሌላው አስቸጋሪ ነገር ከእነዚህ መጻሕፍት ቅጂዎች ውስጥ በአሁኑ ጊዜ ያሉት በጣም ጥቂት መሆናቸው ነው። ከመግደላዊት ማርያም ወንጌል ውስጥ በአሁኑ ጊዜ የሚገኙት ሦስት ቁርጥራጮች ብቻ ናቸው፤ ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱ ትናንሽ ቁርጥራጮች ሲሆኑ በአንጻራዊ ሁኔታ ሲታይ ትንሽ ረዘም የሚለው ደግሞ ዋናው ቅጂ ላይ የሚገኘውን ሐሳብ ግማሽ ያህል ብቻ የያዘ ነው። ከዚህም በላይ ባሉት ጥንታዊ ቅጂዎች መካከል የጎላ ልዩነት አለ።