የግርጌ ማስታወሻ a በመጀመሪያው የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂ ላይ ይሖዋ የሚለው ስም ወደ 7,000 ጊዜ ገደማ ይገኛል። ይህ ስም “መሆን የሚያስፈልገኝን እሆናለሁ” የሚል ትርጉም አለው። (ዘፀአት 3:14 NW) አምላክ ዓላማውን ለመፈጸም መሆን የሚያስፈልገውን ሁሉ መሆን ይችላል። በመሆኑም ይህ ስም፣ አምላክ ዓላማውን ምንጊዜም እንደሚፈጽምና የገባውን ማንኛውንም ቃል እንደሚጠብቅ ዋስትና ይሰጠናል።