የግርጌ ማስታወሻ a በጥንት ጊዜ እንግዳ ሲመጣ ጠቦት ማረድ የተለመደ ነበር። ሆኖም ጠቦት መስረቅ ወንጀል ስለነበር እንዲህ ዓይነቱን ድርጊት የፈጸመ ሰው አራት እጥፍ መክፈል ይጠበቅበታል። (ዘፀአት 22:1) ዳዊት፣ ባለጠጋው ሰው ጠቦቱን ከድሃው መውሰዱ ርኅራኄ የጎደለው ድርጊት እንደፈጸመ የሚያሳይ እንደሆነ ተሰምቶት ነበር። ባለጠጋው ከድሃው ሰው ጠቦቱን መውሰዱ ቤተሰቡ የሚያገኘውን ወተት፣ ሱፍ ሌላው ቀርቶ ወደፊት ብዙ በጎችን ሊያረባበት የሚችልበትን አጋጣሚ ሁሉ ያሳጣዋል።