የግርጌ ማስታወሻ
b አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሑራን “ቍርበት ስለ ቍርበት ነው” የሚለው አገላለጽ ኢዮብ የራሱ ቍርበት ወይም ሕይወት እስካልተነካ ድረስ የልጆቹና የእንስሶቹ ቁርበት ወይም ሕይወት ቢያልፍ ምንም እንደማይመስለው የሚያመለክት ሊሆን እንደሚችል ይናገራሉ። ሌሎች ደግሞ ይህ አነጋገር፣ አንድ ሰው ሕይወቱን ለማዳን ሲል ከቍርበቱ የተወሰነውን ለማጣት ፈቃደኛ ሊሆን እንደሚችል የሚያጎላ እንደሆነ ይሰማቸዋል። ለምሳሌ ያህል፣ አንድ ሰው ጭንቅላቱ እንዳይመታ በእጁ ሊመክት በሌላ አባባል ቍርበቱን ወይም ሕይወቱን ለማትረፍ ሲል ከቍርበቱ የተወሰነውን ለማጣት ፈቃደኛ ሊሆን ይችላል። ይህ ምሳሌያዊ አነጋገር ትርጉሙ ምንም ይሁን ምን፣ ኢዮብ ሕይወቱን ለማትረፍ ሲል ማንኛውንም ነገር መሥዋዕት ለማድረግ ፈቃደኛ እንደሚሆን የሚጠቁም መሆኑ ግልጽ ነው።