የግርጌ ማስታወሻ
b የዚህ “ለስለስ ያለ ድምፅ” ምንጭ ይሖዋ በ1 ነገሥት 19:9 ላይ የሚገኘውን ‘ቃሉን’ ለማስተላለፍ የተጠቀመበት መንፈሳዊ አካል ሳይሆን አይቀርም። ይህ መንፈሳዊ አካል የአምላክ ወኪል በመሆኑ በቁጥር 15 ላይ የተጠቀሰው “እግዚአብሔር” ተብሎ ነው። ይህም ይሖዋ እስራኤላውያንን በምድረ በዳ ለመምራት የተጠቀመበትንና “ስሜ በርሱ ላይ ነው” በማለት አምላክ የተናገረለትን መንፈሳዊ አካል ያስታውሰን ይሆናል። (ዘፀአት 23:21) እውነት ነው፣ ስለዚህ ጉዳይ በእርግጠኝነት መናገር አንችልም፤ ያም ሆኖ ኢየሱስ ሰው ከመሆኑ በፊት “ቃል” ማለትም ይሖዋ ከአገልጋዮቹ ጋር ባለው ግንኙነት ልዩ ቃል አቀባይ ሆኖ እንዳገለገለ ልብ ማለት ይገባል።—ዮሐንስ 1:1