የግርጌ ማስታወሻ
b ጳውሎስ የጻፈው ይህ ሐሳብ በዘፍጥረት 3:15 ላይ ተመዝግቦ የሚገኘውን ከጊዜ በኋላ ዲያብሎስ እንደሚጠፋ የሚጠቁመውን የመጀመሪያውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ያስታውሰናል። ጳውሎስ፣ ዲያብሎስ የሚደርስበትን ጥፋት ለማመልከት የተጠቀመበት የግሪክኛ ቃል “አንድን ነገር በመጨፍለቅ ማድቀቅ፣ መሰባበር፣ ድምጥማጡን ማጥፋት” የሚል ትርጉም ያስተላልፋል።—ቫይንስ ኮምፕሊት ኤክስፖዚተሪ ዲክሽነሪ ኦቭ ኦልድ ኤንድ ኒው ቴስታመንት ወርድስ