የግርጌ ማስታወሻ
d ቀዳማዊ ጠረክሲስ ስሜቱ በቅጽበት የሚለዋወጥ ግልፍተኛ ሰው በመሆኑ ይታወቃል። ግሪካዊው ታሪክ ጸሐፊ ሄሮዶተስ፣ ጠረክሲስ ከግሪክ ጋር ስላደረገው ጦርነት በጻፈው ታሪክ ላይ ስለ ንጉሡ ባሕርይ የሚገልጹ አንዳንድ ምሳሌዎችን ጠቅሷል። ንጉሡ በሄሌስፖንት ወሽመጥ ላይ ድልድይ እንዲሠራ ትእዛዝ ሰጥቶ ነበር። ድልድዩን ማዕበል ባፈረሰው ጊዜ ጠረክሲስ መሃንዲሶቹ አንገታቸው እንዲቀላ ያዘዘ ከመሆኑም ሌላ ከፍ ባለ ድምፅ እርግማን በሚታወጅበት ጊዜ አገልጋዮቹ ውኃውን በመግረፍ ሄሌስፖንትን “እንዲቀጡ” መመሪያ ሰጥቷል። ከዚህ ዘመቻ ጋር በተያያዘ ባለጸጋ የሆነ አንድ ሰው ልጁ ከውትድርና ግዳጅ ነፃ እንዲሆን በለመነው ጊዜ ጠረክሲስ ልጁ ለሁለት እንዲቆረጥ ያዘዘ ከመሆኑም ሌላ አስከሬኑን ሌሎች እንዲያዩት በማድረግ መቀጣጫ እንዲሆን አድርጓል።