የግርጌ ማስታወሻ
a ይሖዋ፣ አባታችን እንደሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ጊዜ ተጠቅሷል። ለምሳሌ ያህል፣ ኢየሱስ ስለ ይሖዋ ሲናገር “አባት” እና “አብ” በሚሉት ቃላት በተደጋጋሚ ይጠቀም ነበር፤ እነዚህን ቃላት በመጀመሪያዎቹ ሦስት ወንጌሎች ውስጥ ከ60 ጊዜ በላይ እንዲሁም በዮሐንስ ወንጌል ላይ ብቻ 100 ጊዜ ያህል እናገኛቸዋለን። ሐዋርያው ጳውሎስም በጻፋቸው ደብዳቤዎች ላይ ስለ አምላክ ሲናገር እነዚህን ቃላት ከ40 ጊዜ በላይ ተጠቅሟል። ይሖዋ፣ አባታችን የተባለው ሕይወታችንን ያገኘነው ከእሱ ስለሆነ ነው።