የግርጌ ማስታወሻ
b ኑኃሚን እንደገለጸችው ይሖዋ ደግነት የሚያሳየው በሕይወት ላሉት ብቻ ሳይሆን ለሞቱትም ጭምር ነው። ኑኃሚን ባሏንና ሁለቱንም ወንዶች ልጆቿን በሞት አጥታለች። ሩትም ባሏን በሞት ተነጥቃለች። እነዚያ ሟች ሦስት ወንዶች በሁለቱ ሴቶች ሕይወት ውስጥ ትልቅ ቦታ እንደነበራቸው ጥርጥር የለውም። ሟቾቹ፣ ኑኃሚንን እና ሩትን ይወዷቸው ስለነበር እንክብካቤ እንዲደረግላቸው እንደሚፈልጉ የታወቀ ነው፤ በመሆኑም ለእነዚህ ሴቶች የሚደረግ ማናቸውም የደግነት ድርጊት ለሟቾቹ እንደተደረገ የሚቆጠር ነው።