የግርጌ ማስታወሻ
b ላሜሕ ለልጁ ኖኅ የሚል ስም ያወጣለት ሲሆን ትርጉሙም “እረፍት፤ ማጽናኛ” ማለት ሳይሆን አይቀርም። በተጨማሪም ላሜሕ፣ ኖኅ የሰው ዘር በተረገመችው ምድር ላይ ከሚደርስበት ድካምና ልፋት እረፍት እንዲያገኝ በማድረግ ከስሙ ትርጉም ጋር የሚስማማ ተግባር እንደሚፈጽም ትንቢት ተናግሯል። (ዘፍጥረት 5:28, 29) ሆኖም ላሜሕ ቀደም ብሎ በመሞቱ ይህ ትንቢት ሲፈጸም ማየት አልቻለም።