የግርጌ ማስታወሻ
d እርግጥ ነው፣ የአምላክ ቃል “ለመረዳት የሚከብዱ” የሚመስሉ ትምህርቶችንም ይዟል፤ ከእነዚህ መካከል ጳውሎስ የጻፋቸው አንዳንድ ሐሳቦች ይገኙበታል። ይሁንና የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎችን በሙሉ የመራቸው የአምላክ ቅዱስ መንፈስ ነው። ይኸው መንፈስ በዛሬው ጊዜ የምንገኝ እውነተኛ ክርስቲያኖች መለኮታዊ እውነቶችን እንድንገነዘብ አስችሎናል፤ ይህ መንፈስ የመረዳት ችሎታችን ውስን ቢሆንም፣ ‘የአምላክ ጥልቅ ነገሮች’ እንኳ ይበልጥ ቀላልና ግልጽ እንዲሆኑልን አድርጓል።—2 ጴጥ. 3:16, 17፤ 1 ቆሮ. 2:10