የግርጌ ማስታወሻ
a ማኑስክሪፕትስ ኦቭ ዘ ግሪክ ባይብል የተሰኘው መጽሐፍ እንደገለጸው ፔሊዮግራፊ “ጥንታዊ ጽሑፎችን የሚያጠና የሳይንስ መስክ ነው።” ጊዜ እያለፈ ሲሄድ የእጅ ጽሑፍ አጣጣል ይለወጣል። በመሆኑም የተጻፉበት ዘመን በአስተማማኝ ሁኔታ የታወቁ ሰነዶችን፣ አዲስ በተገኘው ጥንታዊ ቅጂ ላይ ካለው የእጅ ጽሑፍ አጣጣል ጋር በማነጻጸርና በመካከላቸው ያለውን የእጅ ጽሑፍ ልዩነት በማየት አዲስ የተገኘውን ጥንታዊ ቅጂ ዕድሜ ማወቅ ይቻላል።