የግርጌ ማስታወሻ
b ሲሳራ አብዛኛውን ጊዜ ከውጊያ ሲመለስ ልጃገረዶችን፣ እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ ለእያንዳንዱ ወታደር ከአንድ በላይ ልጃገረዶች ማርኮ ይመጣ እንደነበር ዲቦራ ካቀናበረችው መዝሙር መረዳት ይቻላል። (መሳፍንት 5:30) እዚህ ጥቅስ ላይ “ልጃገረድ” የሚለው ቃል “ማህፀን” የሚል ቀጥተኛ ትርጉም አለው። ይህ አገላለጽ እነዚህ ሴቶች የሚፈለጉት ለፆታ ግንኙነት ብቻ እንደነበር ይጠቁማል። ሴቶችን አስገድዶ መድፈር የተለመደ ነበር።