የግርጌ ማስታወሻ a “ወንድሞች” የሚለው አጠራር በጉባኤ ውስጥ ያሉ ሴቶችንም ይጨምራል። ጳውሎስ ደብዳቤውን የጻፈው በሮም ለሚገኙ “ወንድሞች” ቢሆንም ይህን ያለው እህቶችንም በአእምሮው ይዞ ነው። በደብዳቤው ላይ አንዳንድ እህቶችን በስም መጥቀሱ ይህን ያሳያል። (ሮም 16:3, 6, 12) ቀደም ካሉት ዘመናት ጀምሮ መጠበቂያ ግንብ መጽሔት በጉባኤ ውስጥ ያሉ ክርስቲያኖችን ለመግለጽ ‘ወንድሞችና እህቶች’ የሚለውን አጠራር ሲጠቀም ቆይቷል።