የግርጌ ማስታወሻ b አርማጌዶንን በሕይወት ከሚያልፉ ሰዎች መካከል የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎች እንደሚኖሩ መጠበቁ ምክንያታዊ ነው። ኢየሱስ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት “ማንኛውንም ዓይነት ሕመም” ፈውሷል፤ ይህም አርማጌዶንን በሕይወት ለሚያልፉ ሰዎች ምን እንደሚያደርግ የሚያሳይ ናሙና ነው። (ማቴ. 9:35) ትንሣኤ የሚያገኙ ሰዎች ጤናማና የተሟላ አካል ይዘው እንደሚነሱ ምንም ጥርጥር የለውም።