የግርጌ ማስታወሻ
a የአርኪኦሎጂ ባለሙያዎች በኢያሪኮ ፍርስራሽ ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው የእህል ክምችት አግኝተዋል፤ ይህም ከተማዋ ለረጅም ጊዜ ተከባ እንዳልቆየችና የእህል ክምችቷ እንዳላለቀ የሚጠቁም ነው። እስራኤላውያን ከኢያሪኮ ምንም ነገር እንዳይወስዱ ታዘው የነበረ ከመሆኑ አንጻር ከተማዋን የወረሩት በትክክለኛ ወቅት ላይ ነው ማለት ይቻላል፤ ምክንያቱም ጊዜው የመከር ወቅት በመሆኑ ከከተማዋ ውጭ በማሳዎች ላይ የተትረፈረፈ እህል ማግኘት ይችሉ ነበር።—ኢያሱ 5:10-12