የግርጌ ማስታወሻ
a እንደ እውነቱ ከሆነ በአስተሳሰቡ ላይ ማንም ተጽዕኖ እንዳላሳደረበት የሚያስብ ሰውም እንኳ በሆነ አካል ተጽዕኖ ሥር መሆኑ አይቀርም። ሰዎች እንደ ሕይወት አመጣጥ ባሉ የተወሳሰቡ ጉዳዮችም ሆነ የሚለብሱትን ልብስ እንደመምረጥ ባሉ ቀላል ጉዳዮች ረገድ በተወሰነ መጠንም ቢሆን የሌሎች አስተሳሰብ ተጽዕኖ ያደርግባቸዋል። ሆኖም እያንዳንዳችን ተጽዕኖ እንዲያደርግብን የምንፈቅደው ማን እንደሆነ መምረጥ እንችላለን።