የግርጌ ማስታወሻ
d የግርጌ ማስታወሻ፦ “አትፍራ” የሚለው ቃል ሦስት ጊዜ ማለትም በኢሳይያስ 41:10, 13 እና 14 ላይ ተጠቅሶ ይገኛል። በተጨማሪም እነዚህ ጥቅሶች “እኔ” (ይሖዋን ያመለክታል) የሚለውን ቃል በተደጋጋሚ ይጠቅሳሉ። ኢሳይያስ “እኔ” የሚለውን ቃል በተደጋጋሚ እንዲጠቀም ይሖዋ በመንፈሱ የመራው ለምንድን ነው? አንድን አስፈላጊ እውነታ ይኸውም ፍርሃታችንን ማሸነፍ የምንችለው በይሖዋ በመታመን ብቻ እንደሆነ ጎላ አድርጎ ለመግለጽ ነው።