የግርጌ ማስታወሻ b ተጨማሪ ማብራሪያ፦ ይሖዋ የራሳችንን አስተሳሰብ፣ ስሜትና ድርጊት በመመርመር ራሳችንን የመዳኘት ችሎታ ሰጥቶናል። መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ችሎታ “ሕሊና” በማለት ይጠራዋል። (ሮም 2:15፤ 9:1) በመጽሐፍ ቅዱስ የሠለጠነ ሕሊና የሚባለው የምናስበው፣ የምናደርገው ወይም የምንናገረው ነገር ጥሩ ወይም መጥፎ መሆኑን ለመዳኘት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን የይሖዋን መሥፈርቶች የሚጠቀም ሕሊና ነው።