የግርጌ ማስታወሻ
a ይሖዋ አፍቃሪ፣ ጥበበኛና ታጋሽ የሆነ አባት ነው። የፍጥረት ሥራዎቹ እና የሞቱ ሰዎችን ለማስነሳት ያለው ዓላማ እነዚህን ባሕርያቱን በግልጽ ያሳያሉ። በዚህ ርዕስ ላይ፣ ትንሣኤን በተመለከተ የሚነሱብንን አንዳንድ ጥያቄዎች እንመረምራለን፤ በተጨማሪም የትንሣኤ ተስፋ ስለ ይሖዋ ፍቅር፣ ጥበብና ትዕግሥት ምን እንደሚያስተምረን እንዲሁም ይህን ማወቃችን ምን እንዲሰማን ሊያደርግ እንደሚገባ እንመለከታለን።