የግርጌ ማስታወሻ a “ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር” ተብሎ የተጠራው ሐዋርያው ዮሐንስ እንደሆነ ይታመናል። (ዮሐ. 21:7) ስለዚህ ገና ከወጣትነቱ ጀምሮ ብዙ የሚወደዱ ባሕርያት እንደነበሩት መገመት እንችላለን። ከዓመታት በኋላ ይሖዋ፣ ይህ ሐዋርያ ስለ ፍቅር ብዙ እንዲጽፍ አድርጓል። በዚህ ርዕስ ላይ ዮሐንስ የጻፋቸውን አንዳንድ ሐሳቦች መለስ ብለን እንመለከታለን፤ እንዲሁም ከእሱ ምሳሌ ምን እንደምንማር እናያለን።