የግርጌ ማስታወሻ
a ይሖዋ ከሌሎች ጋር አያወዳድረንም። ያም ቢሆን አንዳንዶቻችን ራሳችንን ከሌሎች ጋር ማወዳደር ይቀናን ይሆናል፤ በዚህም ምክንያት ለራሳችን ዝቅተኛ አመለካከት እናዳብር ይሆናል። ራሳችንን ከሌሎች ጋር ማወዳደር ጎጂ የሆነው ለምን እንደሆነ በዚህ ርዕስ ውስጥ እንመለከታለን። በተጨማሪም የቤተሰባችን አባላት እንዲሁም በጉባኤያችን ውስጥ ያሉ ወንድሞችና እህቶች ስለ ራሳቸው የይሖዋ ዓይነት አመለካከት እንዲኖራቸው ልንረዳቸው የምንችለው እንዴት እንደሆነ እንመረምራለን።