የግርጌ ማስታወሻ
a አንድ የቤተሰባችን አባል ይሖዋን ሲተው በእጅጉ እንደምናዝን የታወቀ ነው። እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ሲያጋጥመን አምላካችን ምን እንደሚሰማው በዚህ ርዕስ ውስጥ እንመለከታለን። በተጨማሪም ታማኝ የሆኑት የቤተሰብ አባላት ይህ ሁኔታ የሚያስከትለውን ሥቃይ ለመቋቋምና ጠንካራ መንፈሳዊነት ይዘው ለመቀጠል ምን ማድረግ እንደሚችሉ እንመለከታለን። ከዚህም ሌላ፣ በጉባኤው ውስጥ ያሉ በሙሉ ለቤተሰቡ ማጽናኛና ድጋፍ መስጠት የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ይህ ርዕስ ያብራራል።