የግርጌ ማስታወሻ
a ይሖዋ ከማንም በላይ የምንቀርበው ወዳጃችን ነው። ከእሱ ጋር ያለንን ወዳጅነት ከፍ አድርገን እንመለከተዋለን፤ ስለ እሱ ይበልጥ ማወቅም እንፈልጋለን። አንድን ሰው በደንብ ለማወቅ ጊዜ ይጠይቃል። ከይሖዋ ጋር ያለን ዝምድና እየተጠናከረ እንዲሄድ በምናደርገው ጥረትም ይህ እውነት ነው። ሆኖም ሕይወታችን በውጥረት የተሞላ ነው። ታዲያ ወደ ሰማዩ አባታችን ለመቅረብ የሚሆን ጊዜ ለማግኘት ምን ማድረግ እንችላለን? ይህን ማድረጋችንስ የሚጠቅመን እንዴት ነው?