የግርጌ ማስታወሻ
a የቀድሞ ሕይወታችንና አስተዳደጋችን ምንም ይሁን ምን “አዲሱን ስብዕና” መልበስ እንችላለን። ይህ እንዲሆን ግን የአስተሳሰብ ለውጥ ለማድረግና እንደ ኢየሱስ ለመሆን የምናደርገውን ጥረት መቀጠል አለብን። በዚህ ርዕስ ላይ የኢየሱስን አስተሳሰብና ምግባር የሚያሳዩ ምሳሌዎችን እንመለከታለን። ከተጠመቅን በኋላም የእሱን ምሳሌ መከተላችንን መቀጠል የምንችለው እንዴት እንደሆነም እናያለን።